lnu.sePublications
Change search
CiteExportLink to record
Permanent link

Direct link
Cite
Citation style
  • apa
  • ieee
  • modern-language-association-8th-edition
  • vancouver
  • Other style
More styles
Language
  • de-DE
  • en-GB
  • en-US
  • fi-FI
  • nn-NO
  • nn-NB
  • sv-SE
  • Other locale
More languages
Output format
  • html
  • text
  • asciidoc
  • rtf
የመገናኛ ብዙሃን የርስ በርስ ቁጥጥርን ተግባራዊ ማድረግያ መንገድ በኢትዮጵያ
2021 (English)Report (Other (popular science, discussion, etc.))
Sustainable development
SDG 16: Promote peaceful and inclusive societies for sustainable development, provide access to justice for all and build effective, accountable and inclusive institutions at all levels
Abstract [en]

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን የቁጥጥር ስርዓት ምን መምሰል አለበት በሚለው ሃሳብ ላይ የሚነሳው ክርክር በሕግ ምላሽ ያገኘው በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2021 ነው፡፡ በአስገዳጅ ሕግ ላይ ያልተመሰረተ የመገናኛ ብዙሃን የጋራ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር እድል ሰጥቶታል፡፡ የተጋጋለ ብሔርተኝነት፣ የማህበረሰብ ግጭት እና የዜጎች መፈናቀል የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሽግግር በተደጋጋሚ እየፈተነ ያለ ጉዳይ ቢሆንም ሃገሪቱ ለበርካታ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ፈቃጅና አካታች የሆነ ምህዳር በመፍጠር ላለፉት ሦስት ዓመታት በዲሞክራሲ ሸግግር ውስጥ በማለፍ ላይ ትገኛለች፡፡ በሂደት ላይ ያለውን አካታች የለውጥ ፕሮግራም እና የፖሊሲ ስነ ምህዳር መስፋት ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ተዋንያን በሀገሪቱ የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓት ውስጥ ያላቸውን ሚና በማሳደግ እንዲሁም የርስ በርስ የቁጥጥር አካሉ በአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን የአስተዳደር ስርአት ውስጥ ያለውን የቁጥጥር ሚና ለማሳወቅ የሚረዱ የህግና የአስተዳደር እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ለሶስት አስርት ዓመታት ያህል በአምባ ገነን የመንግስት ስርዓት ውስጥ ሆን ተብሎ ሲዳከም በቆየው የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ውስጥ እንዴት ጠንካራና ውጤታማ የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓት መገንባት ይቻላል የሚለው ጥያቄ አሁንም መሰረታዊ ተግዳሮት ነው፡፡ በአሁን ጊዜም ቢሆን ቀደም ሲል የነበረውን የተቋም ባህል በማስቀጠል ረገድ በአዲስ መልክ ጥብቅ የቁጥጥር ስርዓትን የመዘርጋት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ እየቀጠለ የመጣው የዘርፉ በፖለቲካ ባለቤትነት ተፅእኖ ስር የመውደቅ ሁኔታ የዘርፉን ታአማኒነት በመሸርሸር፤ የህዝብ አመኔታን ለማግኘት የሚጓዝበትን መንገድ ይበልጥ ውስብስብ እያደረገው ይገኛል፡፡

አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መገናኛ ብዙሃን ከፖለቲካ ሃይሎች ባለቤትነት ነጻ እንዲሆኑ ቢደነግግም በተግባር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በዜና ዘጋቢ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ውስጥ ከፍተኛውን የባለቤትነት ድርሻ ይዞ ይገኛል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢሆኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መገናኛ ብዙሃንን በገንዘብ በመደገፍ፣ በማንቀሳቀስና በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠንካራ፣ ሙያዊ ብቃትን የተላበሰ እና የስነ-ምግባር መርሆችን የሚያከብር የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ መፍጠር እንዲሁም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓት የመዘርጋት ሂደት ረጅም ጊዜ የሚወሰድ አድካሚ ስራ ነው፡፡

የርስ በርስ መገማገሚያ መድረክ ለመፍጠር በዘርፉ ተዋናዮችና አለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት አማካኝነት ለአስርት አመታት ያህል ከተደረገ አድካሚ ጥረት በኋላ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በ2018 ዓ.ም እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ወደ 50 የሚጠጉ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የምክር ቤቱ አባል ሆነዋል፡፡ ነገር ግን ምክር ቤቱ አሁንም ቢሆን ስራውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ በትግል ላይ ይገኛል፡፡

በስራ ላይ ያለ እና ተግባራዊ የሆነ የርስ በርስ የቁጥጥር ስርአት የመቋቋሙ አስፈላነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ምክር ቤቱ በአሁን ጊዜ ባለው አሰራርና ቁመና ብቻ አገልግሎቱን በብቃት ሊሰጥ አይችልም፡፡ የመገናኛ ብዙሃን የርስ በርስ ቁጥጥር ስርአት ለሀገሪቱ አዲስ በመሆኑ የቁጥጥር ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የዘርፉ ተዋንያንን በሙሉ ቀስ በቀስ ወደ መዋቅሩ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማረጋገጥ እንዲሁም የሀገር ውስጥ፣ ቀጠናዊ እና አለም አቀፍ ልምዶችን በመውሰድ የርስ በርስ የቁጥጥር ስርአት በኢትዮጵያ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል የጋራ መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

አሁን ባለንበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓት የማጠናከር ስራ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እንደተደነገገው የስነ-ምግባር መመሪያውን ተግባራዊነት ለማስፈፀም እስከቻሉ ድረስ ከመንግስት የቁጥጥር ስርዓት ውጪ የሆኑ አማራጭ የቁጥጥር ስርዓቶች እንዲኖሩ ይፈቀዳል እንዲሁም ይበረታታል፡፡

በአዋጁ ትርጓሜ መሰረት የርስ በርስ ቁጥጥር ስርአት ማለት ‹‹የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው የሚገዙበትን፣ የሙያ ሥነ ምግባርና የመልካም አሠራር ደንብ የሚያወጡበትን፣ የዘርፈን የሙያ ብቃት የሚያሳድጉበትን እና የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ቅሬታዎች የሚያስተናግዱበትን አሰራር በመዘርጋት ራሳቸውን ለህዝቡ ተጠያቂ አድርገው እርስ በእርስ የሚተራረሙበት ሂደት ነው፡፡››

ይህም የጥናት ፅሁፍ የሚዳስሰው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የርስ በርስ መገማገሚያ ስርዓትን በመዘርጋት፣ የህዝብ ቅሬታን ተቀብሎ በማስተናገድ እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ እያጋጠሙ ያሉ ዋና ዋና ችግሮችንና እና ተስፋ ሰጪ እድሎችን ነው፡፡

Place, publisher, year, edition, pages
Kalmar, Sweden: Fojo: Media Institute , 2021. , p. 53
National Category
Media Studies
Research subject
Media Studies and Journalism
Identifiers
URN: urn:nbn:se:lnu:diva-119372OAI: oai:DiVA.org:lnu-119372DiVA, id: diva2:1737503
Available from: 2023-02-16 Created: 2023-02-16 Last updated: 2023-02-17Bibliographically approved

Open Access in DiVA

fulltext(4130 kB)193 downloads
File information
File name FULLTEXT01.pdfFile size 4130 kBChecksum SHA-512
0e440a5586ade2de396efdb04ce796b7a926e2c8737a3b2e43059a42f60dbe33eed047253f397204b06b604f4ead672add4c37052fe37ac7306ae26e8b73b957
Type fulltextMimetype application/pdf

Media Studies

Search outside of DiVA

GoogleGoogle Scholar
Total: 193 downloads
The number of downloads is the sum of all downloads of full texts. It may include eg previous versions that are now no longer available

urn-nbn

Altmetric score

urn-nbn
Total: 373 hits
CiteExportLink to record
Permanent link

Direct link
Cite
Citation style
  • apa
  • ieee
  • modern-language-association-8th-edition
  • vancouver
  • Other style
More styles
Language
  • de-DE
  • en-GB
  • en-US
  • fi-FI
  • nn-NO
  • nn-NB
  • sv-SE
  • Other locale
More languages
Output format
  • html
  • text
  • asciidoc
  • rtf